በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ማለትም ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡- ሎት 1 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ እንዲሁም ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ለባህል ቡድኖች የሚያገለግል) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
  5. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የእቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ጎ/ቆ/ወ/ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊቱን ከተገለፀ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋዉን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከታህሳስ 20 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 05/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ጥር 05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታውን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ጥር 05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት። ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለ መስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር መቀነስ ይችላል እና ማንኛውም ተጫራች ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃውን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ሊያቀረብ ነው፡፡
  15. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here