በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለጃ/ወ/ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቢሮ G+1 ፎቅ ለማስገንባት የህንጻ ዲዛይን እና የሥራ ዝርዝር እንዲሁም የአፈር ጥናት የሚሰራ የአማካሪ መሃንዲስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሥራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከታህሳስ 20/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 10/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 ጥር 12/2018 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሰነዶች እና አጠቃላይ ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

