ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
50

በቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኝ ሴ/መስሪ ቤቶች  በ2018 የበጀት ዓመት   አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች  የተዘረዘሩትን   በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ  መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2  ኤሌክትሮኒክ፣ ሎት 3 የውሃ እቃ፣ ሎት 4 የቢሮ አጥር ግንባታ፣ ሎት 5  የአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ስለሆነም የሚመለከታቹህ ተጫራቾች  ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚፈለገውን እቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና በመሂ 1 የተቆረጠ ጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 04/2018 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጥር 05/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ጥር 05/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. የመክፈቻ ቀን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ጥር 05/ 2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  2. ሎት 2 ኤሌክትሮኒክ ጥር 05/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
  3. ሎት 3 የውሃ እቃ ጥር 06/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  4. ሎት 4 የቢሮ አጥር ግንባታ ጥር 12/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  5. ሎት 5 የአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ጥር 12/02018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ቋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስከረብ አለበት፡፡
  7. እቃውን የምንረከበው በያዝነው የበጀት ልክ ነው፡፡
  8. አሸናፊ የሚለየው በሎት ነው፡፡
  9. ከላይ ደረጃ 9 ተብሎ የተገለፀው ለቢሮ አጥር ግንባታ እና ለአሶል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የግንባታ ጨረታዉ 21 ቀን ሚዉል ይሆናል፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ወይም ቋራ ወ/ገን/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 271 02 69 /00 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here