ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
67

ቁጥር 11/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ የስቱዲዮ ሀ እና ለ ኮንትሮል ሩም የኢንቴረር ስራን ደረጃ 8 ብቻ  የማጠናቀቅ ስራ /የማስዋብ/ ፈቃድ ያለቸዉን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የከተማ ልማት የብቃት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት፣  ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው  በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ  21 ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ  ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት  አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106  መዉሰድ  ይችላሉ፡፡  የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ  በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን  በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉትን የኢንቴረር ሥራ ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here