ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት አመት ለፍ/ቤቱ አገልግሎት የሚሰጡ ሎት1∙አላቂ የፅፈት መሳሪያዎች፣ሎት2∙ቋሚ እቃዎች፣ ሎት3∙ የህትመት ስራዎች፣ ሎት4∙ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5∙ ማሽነሪዎች (የኤሌክትሮኒክስ)  እቃዎች፣ ሎት6 ሀ∙ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 6ለ∙ የደንብ ልብስ ብትን ጨርቆች እንዲሁም የመስተንግዶ አገልግሎት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የምስክር ወረቀት ያላችሁ፣ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁና ቲን ያላችሁ፡፡
  2. የምትሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱ አርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማንኛዉም ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
  4. የሞላችሁት እቃ ድምር አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቅድሚያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች ለክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/ 2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
  7. የጨረታውን ሰነድ ከታህሳስ 27/2018 እስከ ጥር 12/2018 ዓ/ም ከጧቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (በሌሉበት) በአንጎት /ወ/ፍ/ቤት ጥር 12/2018 ዓ/ም በ 3፡00 ታሽጎ  በ3፡15 የከፈታል ፡፡ የጨረታ መክፈቻው የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በ3፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ያሸነፉቸውን እቃዎች አ/ወ/ፍ/ ቤት አሁን ተገኝ ከተማ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይገባቸዋል፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፍ/ቤቱ  ሥ/ቁ 09 19 89 54 10/09 21 97 57 90 /09 48 85 84 27 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአንጎት ወረዳ ፍ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here