በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ አስተዳደር ዓባይ በር የህብረት ስራ ማህበር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዩን ኃላፊነቱ የተወሰነ አገልግሎት የሚውል SACCO UNION FINACIAL MANAGEMENT SOFT WARE በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች እንድትሳተፋ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሶፍት ዌር አጠቃላይ የዩኒዬኑን ሁሉንም አይነት የሂሳብ ሪፖርቶች መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- ሶፍት ዌሩ አጠቃላይ የዩኒዬኑን ሁሉንም አይነት ሪፖርቶች መስራት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት (ግሰሰብ) ዩኒዬኑ ባለሙያዎች በቂ የሆነ ስልጠና መስጠት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በዩኒዬኑ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥር 1000019160924 ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋና ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ በታሸገ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ7 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ8ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን በ8 ተኛው ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የዩኒዬኑ ባዘጋጀው ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች አንደአሸነፉ SACCO UNION FACIAL MANAGEMENT SOFI WARE ወድያውኑ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች SACCO UNION ENACIAL MANAGEMENT SOFT WARE በኢትዮጲያ ባሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬኖች ተግባራዊ የሆነና ውጤታማነቱን ከዩኒዬኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 776 04 93 /09 20 50 58 09 መደወል ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ደጀን በአዲሱ መናኻሪያ መግቢያ ከዋናው መስመር አጠገብ ነው፡፡
አባይ በር የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዩን መስሪያ ቤት

