የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት 1ኛ. የቢሮ እና የግቢ ጽዳት፣ 2ኛ. የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ 3ኛ. የኤሌክትሮኒከስ ጥገና እንዲሁም 4ኛ. የመኪና እና የጀኔሬተር ቅባት እና ዘይት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከታህሣስ 27/2018 ዓ/ም እስከ ጥር 11/2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ጥር 12/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ጠ/ፍ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ባሕር ዳር

