ዉራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 01 ፣ ባለስድስት ወለል (B+G+6) ንግድ እና ማይክሮ ፋይናንስ ህንፃ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ (የመሰረት ዉቅር ሥራ ግሬድ ቢም ዉቅር የመሬት ወለል ስላብና ቋሚ ኮለን ሥራ አንደኛ ወለል ኮለንና ስላብ፣ ደረጃ ሥራ ሊፍት) (ከቤዝመንት እስከ የ1ኛ ፎክ ስላብ ድረስ የጉልበት ሥራን ብቻ ለመስራት) ለማከናወን GC-4 እና በላይ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ የጉልበት ኮንትራት ግንባታ ሥራዉን በቁርጥ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታዉ መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጉልበት ኮንትራት ሥራዉን በቁርጥ ዋጋ ለመስራት (ለመገንበት) ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
- GC-4 እና በላይ የሆኑ ተቋራጮች ከዚህ በፊት በፈቃደቸዉ መስራታቻዉን የሚገልጽ የድጋፍ ደብደቤ መንግስታዊ ከሆነ ድርጅት አሊያም ከግል ድርጅት ማህበር ወይም ተቋም መስራታቸዉን እና እየሰሩ መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ ማምጣት የሚችሉ እና አጠቃላይ መስፈርቱን የሚያሞሉ መሆን አለባቸዉ
- ተጫራቾች ለግንባታ የሚያስፈልገዉን የሰዉ ኃይል፣ ማሽነሪ እና የእጅ መሳሪያዎችን አቅርቦት በማሞላት እንዲሁም የሥራ መርሃ ግብር እና ሌሎች ለሥራዉ የሚያስፈልጉ ማንኛዉንም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር ሰርትፊኬት (ቲን) የቫት መክፈያ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት (VAT REGISTRATION CERTIFICATE) እና ከክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም ከፌደራል ከተማና መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የምዝገበ ምስክር ወረቀት፣ ብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናል በማቅረብ ከፎቶ ኮፒዉ ጋር በማገናዘብ ፎቶ ኮፒዉን በመስጠት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታተይ 21 ቀናት ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 17/2018 ዓ.ም ድረስ ቻግኒ ከተማ ዋናዉ ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታዉን ሰነድ መግዘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በመሙላት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒዉን በመለየት የቴክኒካልና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ትክክለኛ የራሳቸዉን እና ያሰሪዉን ድርጅት አድራሻ በመፃፍ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ብሎ ለይቶ በመፃፍ ኮፒዉን እና ኦርጅናሉን በአንድ ትልቅ ፖስታ አድርጎ በማሸግ ልክ እንደ ኦርጅናሉ አድራሻዉን በትክክል በትልቁ ፖስታ በመፃፍ የጨረታዉ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ድረስ ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 18/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ብቻ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት ዋጋ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ጥር 18/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሠዓት በኃላ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ዋኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዋናዉ ዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- አጠቃለይ ሥራዉ የሚሰራዉ እና የሚከፈለዉ በጥቅል በቁርጥ ዋጋ ነዉ፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09 18 55 49 80 /09 30 00 13 98 /09 03 14 99 99 መደወል ይችላሉ፡፡
ዉራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠበና ብድር ዩኒዬን

