በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ምድብ 1∙ እስቴሽነሪ፣ ምድብ2∙ የዉሃ ግንባታ እቃዎች፣ ምድብ3∙ የመንገድ ጥገና ማሽን ኪራይ፣ ምድብ4∙ የስፖርት ትጥቅ፣ ምድብ5∙ በ3771.4 ሜ/ካሬ ቦታ ላይ የሚያርፍ G+3 ህንጻ ዲዛን ስራ፣ ምድብ 6∙ በልጫ ቀበሌ የኤፍቲሲ ግንባታ ስራ ፣ ምድብ7 የትምህርት ቤት ግንባታ ስራ፣ ምድብ 8∙ በዝጓራ ቀበሌ የጤና ጣቢያ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በመደበኛ እና በፕሮጀክት ከተገኘ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ) ሽህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰሩ ስራወችን (የሚገዙ እቃወችን) አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ለእያዳዱ ሰነድ በመክፍል ከግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኝት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ለእስቴሽነሪ ግዥ 40‚000 (አርባ ሽህ)፣ ለዉሃ ግንባታ ማተሪያል ግዥ 45,000 (አርባ አምስት ሽህ)፣ ለመንገድ ጥገና ማሽን ኪራይ 100,000 (አንድ መቶ ሽህ)፣ ለእስፖርት ትጥቅ ግዥ 10,000(አስር ሽህ)፣ ለህንጻ ዲዛን ስራ 6,000 (ስድስት ሽህ)፣ ለኤፍቲሲ ግንባታ ስራ 60,000 (ስልሳ ሽህ)፣ ለትምህርት ቤት ግንባታ ስራ 60,000 (ስልሳ ሽህ) እና ለመጸዳጃ ቤት ግንባታ 20,000 (ሃያ ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሪ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነዉ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ የዉል ማሰከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሪ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር1 ጨረታው በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሸጎ 4፡00 የከፈታ ጨረታው ሲካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የከፈታ ሰርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በአል ቢሆን በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- በሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ ዋና እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ቢፈጠር በነጠላ ዋጋዉ የሚወሰድ ይሆናል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበት ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በእያንዳንዱ ምድብ በጥቅል ድምር ስለሚወዳደር ሁሉንም እቃዎች መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 67 19 18/09 13 77 29 02/09 18 30 30 12 በመደውል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእስቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤ

