በምስ/ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስ/ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጫረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋፋን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡15 ላይ ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 7 50.00 (ሀምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል መውሠድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ሰፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0586610002 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዙትን እቃዎች 20በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አሸናፊው ተቋሙ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ሞጣ ጤና አጠባባቅ ጣቢያ

