በአፈ/ ከሳሽ ቅዱስ ሚካኤል የእቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሾች እነ ማርልኝ በዛ መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ክፍት ቦታ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ የኔነሽ ኪነጥበብ መካከል ተዋስኖ የሚገኝ መኖሪያ ቤት በአቶ ማርልኝ በዛ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት መነሻ ዋጋ ብር 1,848,734 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ስባት መቶ ሰላሳ አራት ብር) ስለሚሸጥ ጨረታው ከታህሳስ 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 28/2018 ዓ.ም ድረስ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ቆይቶ በጥር 29/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 እስከ 6፡30 ስለሚሸጥ ተጫራቾችም ከጨረታ ቀን በፊት የሚጫረተውን ንብረት መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በሲፒኦ አስይዘው በመቅረብ መጫረት ይችላሉ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

