ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 03

0
100

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች እስከ ዝርጋታው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከጫራታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 50 (አምሳ ብር) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ በመግዛት ከግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 86 መዉስድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃዎች በተሰጠዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዕቃ /አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሆኖ የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ በመፈረም ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዉሎ በ16ኛዉ ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በሆስፒታሉ ከግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 86 በሚገኘዉ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታዉ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታዉን ይከፍታል፡፡ የጨረታዉ ሰነድ መግዛት የሚቻለዉ እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ ጨረታዉን በጠቅላላ ዋጋ የሚያወዳድር ሲሆን በአንድ ምድብ ዉስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ዉስጥ ሳይሞሉ መተዉ አይቻልም፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፏቸዉን ዕቃዎች ደጀን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ እና መዘርጋት አለባቸዉ፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸዉ ከ5 ሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበዉ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. የጨረታዉ ተሳታፊዎች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 86 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 776 13 18 መደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here