ግልጽ የጨረታ ማሰታወቂያ

0
38

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ የውሃ እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋያነት መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ከዚህ በላይ የተቀመጡትን የመወዳድሪያ መስፈርቶች ማሞላት የምትችሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሲሆን  በኪን/በገ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ከረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን መ/ቤቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዉስጥ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ብሎ በመለየት በአንድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ ዘወትር በስራ ስዓት ከጠዋቱ ከ2፡30-6፡30 እንዲሁም ከስዓት ከ7፡30-11፡30 ድረስ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዳችሁን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6.  አሸናፊ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  7. አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት የዉል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት ዉል የሚወስደዉ በኪን/በገ/ወ/ፍ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  9. የእቃ እርክክብ ቦታ በኪንፍዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታዉ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሞላት ያለበት ሲሆን ከነጠላ ዋጋዉም ሆነ ከጠቅላላ ዋጋዉ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታዉ ማህተም ከንግድ ሥራ ፈቃዱ ጋር በቀጥታ ተዛማጅ መሆን ይኖርበታል፡፡
  15. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በኪን/በገ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 00 41 59 24 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡

የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here