የፍኖተ ሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም ሎት1∙ ጅኤስ ቧንቧን መገጣጠሚያ፣ ሎት2∙ ኤች ዲፒ መገጣጠሚያ ሎት3∙የቧንቧና መፍቻዎችና የስራ መሳሪያዎች፣ ሎት4∙ ሲአይ መገጣጠሚያ፣ ዲሲአይ መገጣጠሚያና ቆጣሪ፣ ሎት5∙ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት6∙ የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት7∙ የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት8∙ ኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ሎት9∙ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት10∙ የዉሃ ጥራት ኬሚካል ሪኤጀንት፣ ሎት 11∙ እስቴሽነሪ፣ ሎት12∙ የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት13∙ ኤክስትራክተር፣ ሎት14∙ ኩሽኔታ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ለሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ::
- የጨረታ ማስታወቂያዉ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይዉላል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር አራት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ::
- ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም::
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ::
- አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠ/ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (በጥሬ ገንዘብ) ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/አገ/ ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡
- ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ ወይም ሎት በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ ድርጅቱ ኃላፊነትን አይወስድም::
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 058 77 51 387 /00 75/09 23 42 61 23 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የፍኖተሠላም ከ/ዉ/ ፍ/ አገ/ ድርጅት

