ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለነባሩ ጭልጋ ወረዳ አጠቃላይ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1  የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣  ሎት 3 ኤሌክተሮኒክስ፣ ሎት 4 የጣውላ ቤት ሥራዎች፣  ሎት 5 ፈርኒቸር፣ ሎት 6 የህንፃ መሳሪያ ዕቃ፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ፣ ሎት 8  የመኪና ቋሚ  እቃ፣  ሎት 9 የመኪና አላቂ እቃ ሥራዎች ከሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. ግዥው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. በፍትህ ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያለቅድምያ ክፍያ የሚያቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ማወቅ አለበት፡፡
  6. ጨረታ ላይ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልጽ  ህጋዊ ዶክመንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ኦርጅናሉን ለየብቻ በማሸግ ሁለቱንም ፖስታዎች በጥንቃቄ በአንድ ፖስታ በማሸግ በሳጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የሎት ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለእቃ ግዥዎች 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16 ተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ክፍት ሁኖ 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1  በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ሳምፕል ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በማየት የጨረታ ሰነዱን መሙላት አለባቸው፡፡
  14. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ በሚገዛው ዕቃ ላይ 20 በመቶ የመቀነስና 20 በመቶ የመጨመር መብት አለው፡፡
  17. ጨረታው አሸናፊ የሚለየው በጥቅል  ወይም በተናጠል ዋጋ ይሆናል፡፡
  18. አሸናፋው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በነ/ጭ/ወ/ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ማስረከብ አለባቸው፡፡
  19. ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በ058 333 03 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የነባሩ ጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here