ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
37

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት ለምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ /አስ/ጽ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ እና ለምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ቪዲዮ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ  ሰነዳቸዉ ጋር  አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመውሰድ መወዳድር ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ኤሌክትሮኒክስ ቪዲዮ ካሜራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኙት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየው በሎት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 11/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኙት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና  ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጥር 12/2018 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን ጥር 12/2018 ዓ/ም በ00 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታዉ ማሸነፈቸዉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ  ደረሰኝ ማስያዝ እና ንብረቱን ምስ/ደ/ወ/የመንግስት ኮምኒኬሽን/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል እና አስተዳደር ጽ/ቤት ካለው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር  ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here