በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ የፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት የሚገለገልባቸው ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ሥራ እንዲሁም ሎት 5 ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 (ሀያ ብር) በመክፈል በመ/ቤታችን ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ከዋና ገ/ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ/ስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወታበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በ16ኛዉ ቀን 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዚጊያና መክፈቻ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ከሆናችሁ በኋላ የምታቀርቡት ደረሰኝ የድርጅቱ ስም፣ ስማችሁ እና የንግድ ፈቃድ አይነት በህትመት የተዘጋጀዉ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታ ከሚገዛዉ እቃ መጠን በ20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች እቃዉን በሎት /በጥቅል/ የሚፈፀም መሆኑ ታዉቆ በእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይደረጋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የሞላዉን ጠቅላላ ዋጋ ቫቱን ጨምሮ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በማስያዝ ዉል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- የንብረት ርክክቡ የሚፈፀመዉ ፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የማጓጓዣ ወጭን እና የጉልበት ወጭን በተመለከተ አሸናፊ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 24 46 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፋርጣ ወረዳ ፍርድ ቤት

