በደቡብ ጎንደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ የታች ጋይንት ወረዳ ገንዘብና/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ አገልግሎት ለሚሰጣቸው በወረዳው ውስጥ ለሚገኘው ለታች ጋይንት ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በካፒታል በጀት 1. ከሸጥ እስከ ገጣቢት መስክ እና ከቀኛ ደስታ ሜዳ መንገድ ለማሰራት ደረጃ አምስትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች፣ 2. ለታች ጋይንት ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለማህበረሰብ መድሃኒት ቤት ለማስገንባት ከደረጃ ስምንትና በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች፣ 3. ለታች ጋይንት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ቀበሌ 02 አውንዳ ት/ቤት አንድ ብሎክ በ90 ቀናት ውስጥ ለማስገንባት ከደረጃ ስምንትና በላይ ለሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮች፣ 4. በመደበኛ በጀት የህንፃ መሳሪያ፣ 5. ህትመት አቅርቦት እንዲሁም 6. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት እና ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ለግንባታ የሞያ ብቃትና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የአቅረቦትና የግንባታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለግንባታ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ለአቅርቦት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የግንባታና የአቅርቦት ዓይነት 2 በመቶ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በመሂ ı በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆኑ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ተሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ በአንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆይ 15 እና 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የአቅርቦት በ6 ቀን ግንባታ በ22ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ላይ ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት (በሎት) በመሆኑ የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጠቅላላ ድምር ውጤት መሙላት ይኖርበታል፡፡
- የተሞላው የግንባታ ጨረታ ሰነድ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
- የሞላው የግንባታ ዋጋ አርቲሜቲክ ቸክ ተሰርቶ ከመሃንዲስ ግምቱ ሃያ አምስት በመቶ ዝቅ ብሎ ሞልቶ አሸናፊ ሆኖ ቢሸሽ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ ጉዳዩች በነባሩና በተሻሻለው የግዥ መመሪያ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ታ/ጋ/ወ/ግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 02 18 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የታች ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

