ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት1∙የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች ፣ሎት2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት3∙ የፋብሪካ ዉጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ መሆኑን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በሰነዱ ላይ የተሞላው አጠቃላይ ዋጋ ከ200 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች ለሁለቱም አቅርቦቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ (ሁለት መቶ) ብር የማይመለስ ገንዘብ በመክፈል የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ዘወትር በስራ ስዓት ቢሮ ላይ ሰነዱን መዉሰድ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በ16ተኛው ቀን በ3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተቀመጠው ስዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይኖሩም ለመክፈት አያስተጓጉሉም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ-1 በመቁረጥ ኮፒ አድርገዉ በጨረታ ፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ የዉል ማስከበሪያ 10በመቶ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ወይም በነጠላ ዋጋ ነዉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ማንኛውንም ወጭ ያጠቃለለ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከቦታዉ ላይ መጥቶ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን ፣ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  11. የጨረታ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና በጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም ከመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻን ፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  13. መ/ቤቱ ከጨረታ አሸናፊው የሚፈለገውን አገልግሎት ጥራቱን ሳይቀይር በመመሪያዉ መሰረት ሊጨምር (ሊቀንስ) ይችላል፡፡
  14. ግዥ ፈጻሚዉ አካል ከአሸናፊዉ ተጫራች ጋር ዉል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ በተገለፀዉ የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ የአሸናፊዉ ተጫራች የቀረበዉ በዉድድሩ የተገኘዉ ዋጋ ሳይቀየር እሰከ 20በመቶ (ሃያ በመቶ ) ለመቀነስ ወይም ለመጨመር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የአሸናፊው ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነኡ በተገለጸው የአክርቦት መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተጫራቹ የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር ይችላል፡፡
  15. ለበለጠ ማብራሪያ ወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 667 03 89 ደዉሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የወገዳ ከተ/ አስ/ ገ/ጽ/ ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here