ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

የጨረታ ቁጥር፡- የጨረታ ቁጥር EPSS/09/2018

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባሕር ዳር ቅርጫፍ የመድሃኒቶችንና የህክምና መሳሪያዎችን ወደ ተለያዩ ጤና ተቋማት ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአገልግሎት መ/ቤታችን ማግኘት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከታህሳስ 20/2018 እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ21 ኛው ቀን ጥር 10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡40 ባሕር ዳር ከተማ ጣና ሀይቅ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮአችን ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአገልግሎታችን በአካል በመቅረብ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) የጠቅላላውን ዋጋ ብር 2 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  6. ይህ ጨረታ በአገልግሎት መ/ቤታችን የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  7. የጨረታዉ አሸናፊ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  8. የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለአንድ አመት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  9. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 058 226 51 52 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባሕር ዳር ቅርጫፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here