ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
126

የግልጽ ጨረታ ቁጥር አብክመ/ውኢቢ/ግጨ ዕግ/ቁጥር-004/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውኃና ኢነርጅ ቢሮ በአማራ ክልል  በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽህፈት ቤት ለመጠጥ ውኃ ተቋማት በተመደበ በጀት ሎት 1. የጠላቂ ፓምፖች፣ የሰርፌስ ፓምፖች እና ኮንትሮል ፓኔል የዕቃ አቅርቦት ግዥ (ዘጌ ፣ ማንኩሳ፣ ማክሰኝት፣ ሻሁራ፣ አይምባ፣ እስታይሽ፣ አባድራ፣ ገለጎ፣  ደብረማዊ፣ አዳርቃይ፣ አምቦ ሜዳ፣ ጠባሲት፣ ጋሸና፣ ሰቆጣ እና አካይና እንዲሁም ሎት 2. ሶላር ፓኔል የዕቃ አቅርቦት ግዥ (ጃርሶ ጉራች፣ መሻህ፣ አካይና እና አንጀኔ) ሕጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃውን (አገልግሎቶችን) ለማቅረብ በዘርፉ የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅራቢነት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ጨረታ ሰነዱ ማግኙት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት 1 ብር 450,000 (አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ሎት 2 ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል ዋናና ሁለት ቅጅዎች ፋይናሻያል ዋናና ሁለት ቅጅዎች በማሽግ በድምሩ ስድስት ለየብቻ በታሸገ ፓስታዎች እና ቴክኒካል ዋናና ሁለት ቅጅዎች የታሸጉ ፓስታዎች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፓስታ ፋይናሻያል ዋናና ሁለት ቅጅዎች ፖስታዎችን በአንድ እናት ፓስታ በማሸግ ከእንዳንዱ ፓስታ ላይ የድረጀቱ ፊረማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የግዥን ስም በመጻፋ በውኃና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ጥር 13/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን ጨረታ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ ቅጽ መሰረት መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 582 26 24 60 /+251 582 20 08 55 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የውሃና ኢነርጅ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here