የደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት 1ኛ.ለደራ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ጉሀ ቀበሌ ከጎሽዱር እስከ ደንበዛ ማእከል ድረስ 8.265 ኪ.ሜ እንደኛ ደረጃ የገጠር መንገድ፣ 2ኛ. ለደራ ወረዳ መሬት ጽ/ቤት ለግብርና ፑል ላሉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ፤የቢሮ ግንባታ የእጅ ዋጋ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የሙያ ብቃት ያላቸው እና ከአሁን በፊት መንገድ ስራ ሰርተው የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ለመንገድ ስራ ተቋራጭ ደረጃ አምስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- የቢሮ ግንባታ የህንፃ ስራ ተቋራጭ ደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ግዠው ከ200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የስራው አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የስራ አይነት ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን እና ኮፒ በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለጽ ዘወትር በስራ ሰአት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፤ በ22ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን በአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 258 041 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት

