በአፈ/ከሳሽ እነ አለቃ አምሳል ብዙነህ 2ቱ እና በአፈ/ተከሳሽ ወ/ሮ ይሳለሙሽ ልየው መካከል ባለዉ የውርስ ሃብት ንብረት ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ክፍት ቦታ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ደስታ ልየው መካከል የሚገኘው በአቶ ልየው ካሣ ደስታ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመነሻ ዋጋ ብር 884,680 (ስምንት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ብር) ብቻ ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያው ከታህሳስ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 27/2018 ዓ.ም ለ30 ቀን የሚቆይ ሲሆን የሐራጅ ጨረታው ጥር 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6፡00 ጨረታው ተጫርቶ ውጤቱ በዚያው ቀን ጥር 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 የሚገለጽ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

