በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ላሉ ተቋማት የቢሮ ግንባታ ለወረዳዉ ፍትህ ጽ/ቤት እና ፍርድ ቤት G+2 ደረጃ 5 ሙያ ፈቃድ ያላቸዉ፣ ዉሃ ጽ/ቤት ማህበራትና እንስሳት ጽ/ቤት ቢሮ ግንባታ ደረጃ 6 ሙያ ፈቃድ ያላቸዉ የጋማዉበርና አፀደማርያም ቀበሌ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል FIC ግንባታ ደረጃ 6 የሙያ ፈቃድ የላቸዉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና የሙያ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይንት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የግንባታዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥች ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የግንባታዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች ጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ጥር 27/2018 ዓ.ም በ3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 270 05 97 /195 /194 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

