በአሜሪካ የናፐርቪል ኗሪው የ17 ዓመት ታዳጊ በጥርስ መጐርጐሪያ “ቱዝፒክን” ቁመቱ 17 ነጥብ 32 ጫማ የተለካ የአይፍል ታዎር ቅርፅ አምሣያን ሰርቶ በማጠናቀቅ ለድንቃድነቅ መዝጋቢ ድርጅት አቅርቦ የባለ ክብረወሰንነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ዩፒአይ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
ኤሪክ ክላብል የተሰኙው ታዳጊ አባቱ የሲቪል መሀንዲስ ሞያተኛ መሆኑ ቅርጹን ለመስራት እንዳነሳሳው ተናግሮል። በ2021 እ.አ.አ የ12 ዓመት ታዳጊ ሳለ በማጭድ እንጨት እጀታ ስፋቱ 20 ጫማ የተለካ ማማ ሰርቶ በድንቃድንቅ መዝገብ ስሙን ማስፈሩ ነው ለንባብ የበቃው፡፡ የመጀመሪያ ክብረ ወሰኑ ከተሰበረ ጀምሮ ዳግም አዲስ ክብረወሰን ለማስመዝገብ መትጋቱን ነው የተናገረው – ታዳጊው፡፡
የጥርስ መጐርጐሪያ ስንጥሮቹ መጠናቸው አጫጭር እና ቀጫጭን በመሆናቸው የሁለተኛው ስራ ልዩ መገለጫ መሆኑንም ነው ያብራራው፡፡
በያዝነው 2025 እ.አ.አ ጥቅምት ወር የአይፍል ታዎር አምሳያን የሰራው በ20 ሺህ ስንጥሮች ነው።
የምህንድስና ባለሙያው አባቱም የ “አይፍልታዎር” አምሳያው ቅርፅ ከቤታቸው ጀርባ በልጁ ተሰርቶ መመልካቱ እንዳስደሰተው ተናግሯል፡፡
የማማውን ቁመት እና ውርድ ለክቶ በማረጋገጥ ለመዝጋቢ ድርጅቱ ተልኮ የክብረወሰን ምስክር ወረቀት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ነው በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የታህሣስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም


