ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ም/ቤት ህንፃ አስ/አጠ/ ማዕከል የሚያስተዳድረዉን ህንፃ ለካፍቴሪያ ወይም ሬስቶራንት አገልግሎት ማከራየት ይፈልጋል፡፡  ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ  መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም፣ አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ህንፃ ለካፍቴሪያ (ለሬስቶራንት) አገልግሎት ብቻ የሚዉል መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች ከተሸነፋ ያስያዙት ቢድ ቦንድ እንዲለቀቅ በጸሁፍ ሲያሣውቁ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ስራ አፈጻጸም ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፋበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በሚቀጥለው 10 ተከታታይ ቀን  በሲፒኦ (ስፒኦ)  ወይም በጥሬ  ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፡፡ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በገንዘብ ቢሮ እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  11. በጨረታው ለመሣተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  12. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ ፤በዚሁ እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡
  14. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  15. ተጫራቾች አሸናፊ ሆነዉ ስራ ሲጀምሩ የመብራትና ዉሀ ወጭ በራሳቸዉ የሚሸፍኑ መሆን አለባቸዉ፡፡
  16. ተጫራቾች አሸናፊ ሆነዉ ስራ ሲጀምሩ ምድረ ግቢዉን የሚያለማና የሚንከባከብ በራሳቸዉ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  17. በዋጋ መሙያዉ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  18. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ሌሎች በዚህ መመሪያ ያልተገለፁ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ተገዥ ይሆናል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 226 21 51/058 222 14 38 ፖ.ሣ.ቁ 1324

የአብክመ ክልል ም/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here