ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚሰጥ የከርሰ ምድር ውሃ በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ ማስቆፈር (ማሰራት) ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የዘርፉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የሥራ ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 25 በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሥራ ደረጃቸው ከደረጃ 1-6 መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በሥራው ከዚህ በፊት ከሚሞሉበት የሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ መ/ቤታችንም የምስክር ወረቀቱ ትክክለኛነቱን በቀጥታ የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም፣ የድርጅቱ ማህተም፣ አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጥር 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ጨረታው በ22ኛው ቀን ማለትም ጥር 25/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ሥራው የሚያስፈልገው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- አሸናፊው በውሉ መሰረትና በወጣው የመሃንዲስ የሥራ ዝርዝር መሰረት ሰርቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላይ ከተጠቀሱት የስራ ዝርዝር ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሰራት መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ አሽናፊውን የሚለየው በጥቅል ድምር ዋጋ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ሁሉም በጨረታው የተቀመጡትን የሥራ ዝርዝር ዋጋ ሙሉ ለሙሉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 /09 23 22 10 87 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

