ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

በደቡበ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ለፋርጣ ወረዳ ዉሃ ጽ/ቤት ለሰላም አስከባሪዎች እና ለጸጥታ አባላት ለሎጀስቲክ አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 ነጭ ጤፍ፣ አኩሪያ አተር ክክ፣ ምስር ክክ፣ ዘይት ሎት 2. አፍሪዲየቭ የእጅ ፓምፕ እና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁስ፣ ሎት 3 የገጠር ንጹህ ዉሃ ተቋማት የጉልበትና የግንባታ ቁሳቁስን ጨምሮ የቦኖዎች ግንባታ በደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ለማስገንባት በግልጽ ጨረታ የግዥ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ግልጽ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በለይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታስክ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ከዋናዉ ጋር ሊገናዘብ የሚችል ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦድ) ለሚወዳደሩበት ለጤፍ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) አኩሪ አተር ክክ ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) ምስር ክክ ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) ዘይት ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ሎት 2 ለአፍሪዲየቪ የእጅ ጋምፕ እና የግንባታ ቁሳቁስ 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) ሎት 3 ለቦኖዎች ግንባታ ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘበ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ገንዘብ ከመስሪያ ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገዉ ፋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋ/ ጽ/ቤት ብለዉ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ቢሮ ቁጥር በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን፣ ለቦኖዎች ግንባታ በ22ኛዉ ቀን ድረስ ከቀኑ 3፡30 ማስገባት ሲቻል የሚታሸገዉም በዚሁ ስዓት ነዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ክጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን፣ ለቦኖዎች ግንባታ በ22ኛዉ ቀን በ3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ) በተገኙበት ባይገኙም በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊዉ በጥቅል ወይም በተናጠል ሊሆን ይችላል፡፡
  11. ዕቃዎቹን የሚቀርቡት ፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል እና ፋርጣ ወረዳ ዉሃ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ነዉ፡፡
  12. የሚቀርቡት የሎጀስቲክ አቅርቦቶች የአፍሪጊየቨ የእጅ ፓምፕ በሙያተኛ በኮሚቴ ተረጋግጦ የሚገቡ ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here