የመሬት ሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ልማት ባንኪንግና ፋይናንሲንግ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ መሠረት ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 2ኛ ዙር በግልጽ መደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ከቀን ጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ለመኖሪያ እና ለድርጅት በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት ስነድ መግዛት እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ ከጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው 10 የሥራ ቀናት ተቆጥረው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያላቸው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፋ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 06 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 07 72 ወይም 058 221 00 06 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here