ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የሚያገለግል DGPS/GNSS የቅየሳ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 46 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 46 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚታሸግ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ ብሄራዊ የበዓል ቀን  ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈጻጸም  መመሪያው መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
  1. ስለጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 220 93 73 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here