በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት እና በሸበል በረንታ ወረዳ መርገጭ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት የግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስ/ ሂደት የ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ልብሶች፣ ፕላስቲክ ቦት ጫማና ቆዳ ጫማ እንዲሁም ሎት 4 ህንፃ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈልጉ ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፍ ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫራቻ ሰነዳቸዉ ጋር ካለዉ ፖስታ ከዉጭ አያይዞ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ /ፍ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 የዕድዉኃ ከተማ ድረስ በመቅረብ በነፃ መዉስድ ይችላሉ፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል (ዝግ) ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማቸዉንና ማህተማቸዉን በማድረግና በፖስታ በማሸግ ሰነዱን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በሸ/በ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በተጠቀሰዉ ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታዉ መክፈት የማያስቀረዉ መሆኑንና በጨረታዉ ሂደት ለሚወሰኑ ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ አሽናፊዉ በአሸነፈበት ዋጋ መ/ቤቱ ድረስ የአሸነፋቸውን ዕቃዎች በአይነትና በመጠን ቆጥሮ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ከአሸናፊዉ ተጫራች የሚገዛዉ እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ዋጋ ሲሞሉ እያንዳንዱ ሰነድ መሞላት አለበት፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለበት ፊርማቸዉ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱንም በሎት በጠቅላላ ዋጋዉ የሚካሄደዉ ስለሆነ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጠቅላላ ያልሞላ ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- የቸረታዉ አሽናፊ ዉል ሲይዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 247 00 83 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሸበል በረንታ ወረዳ ፍ/ቤት

