በአፈ/ከሳሽ ሽታ ሰውነት እና በአፈ/ተከሳሽ ሽመላስ መኩሪያ መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በአንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መኳንንት፣ በምዕራብ ማረልኝ በዛ፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ንብረት ቦጋለ የአፈ/ተከሳሽ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,977,903 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሶስት ብር) በማድረግ ከጥር 4/2018 ዓ/ም እስከ የካቲት 4/2018 ዓ/ም ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ የካቲት 5/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ተካሂዶ ውጤቱ 8፡00 የሚገለጽ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ያሳውቃል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

