ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
74

ቁጥር-001/2018

የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት  ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውሉ  ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በድምሩ 1,076,756 /አንድ ሚሊዮን ሰባ ስድስት ሽህ ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት/ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን በ 1 ዮኒየን በሥሩ ባሉ 144 መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለመጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ደርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን  እስከ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ባለው  ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡-

  1. የንግድ ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ቢሮ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ና የዘመኑን የመንግስት ግብር መከፈሉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
  2. የገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት የምዝገባ ሰርተፊኬት ቲን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የተሽከርካሪ ዝርዝር ተራ ቁጥር የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፊቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከመምሪያዉ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚወዳደሩበት ሁ/የገ/ህ/ስ/ ዳሞት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ በግብ/ግብ/አቅ/ገጠር ፋይናንሰ ቡድን ቢሮ 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማሰታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 4፡00 ሰነዱን በሳጥኑ ዉስጥ በማስገባት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተዉ በእለቱ በ4፡30 በመምሪያዉ በሚዘጋጅ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  11. መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መምሪያዉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 08 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here