በምሥራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለሚያስፈልቸዉ የግንባታ ሥራዎች እና የእቃ ግዥ ማለትም ሎት 1 አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ የውስጥ ለውስጥ ጥገና፣ ሎት 2 የድልድይ ግንባታ፣ ሎት 3 የኮንስትራክሽን እቃዎች እና ሎት 4 ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 1 እና 2 ለ30 ለተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሎት 3 እና 4 ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማቻ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃዉን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዋጋ መሙያው ላይ ሥርዝ ድልዝ በግልጽ የማይነበብ በፍሎድ የጠፋ ሰነድ ያቀረበ ከዉድድር ዉጭ ይሆናሉ፡፡ ሰነዱ በጥንቃቄ ተሞልቶ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ ህጋዊ ማህተም ሙሉ ስምና ፊርማ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለሎት 1 እና ሎት 2 እስከ 31ኛው ቀን ፣ ለሎት 3 እና 4 እስከ 16 ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ግንባታ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ብቻ ለሎት 2, ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ ሎት 3 ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ እና ለሎት 4 ብር 40,000 (አርባ ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unwonditional Bank Guarantee/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ውድድሩ በምድብ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ የእያንዳንዱ ሎት አሸናፊ የሚለይ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል አንዱንም እቃ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ በሎት 3 እና 4 ላይ በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚፈጥሩት ስህተት ለሚከሰተዉ የገንዘብም ሆነ የጉልበት ኪሳራ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- በሎት 3 እና 4 ላይ የተጠየቀው የእቃ ግዥ የተሞላው ዋጋ ለ40 ቀን ጸንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የጨረታ የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ብቻ አቅርቦ ውል መያዝ የሚችሉ፡፡
- በሎት 2 ላይ ለተጠቀስው ሥራ ከዚህ በፊት ከ 12 ሜትር ስፓን ገርድር ድልድይ ግንባታ ስለመስራታቸው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በሎት 1 ላይ ለመጫረት ደረጃቸው GC BC 5 እና በላይ የሆኑ፡፡
- በሎት 2 ላይ ለመጫረት ደረጃው BC/GC 5 ከዚያ በላይ የሆኑና ለግንባታ ሥራዉ የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችን በባለቤትነትም በኪራይ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው አይነትና (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በትክክል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ ከተማው ውስጥ ባሉት ሴ/መ/ቤቶች ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግንባታ አሸዋ የጨረታ አሸናፊ ድርጅት በተለያዩ ቀበሌዎች ማድረስ የሚችሉ፡፡
- ጨረታዉ ለሎት 3 እና 4 በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ለሎት 1 እና ሎት 2 በ31ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት በወረዳዉ በሚገኘዉ ፍትህ ጽ/ቤት ዉል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 777 04 80 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

