ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
99

በማእከላዊ ጎንደር ዞን መስተዳድር ውስጥ የሚገኘው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጎንደር ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለወረዳው  ሴክተር መ/ቤቶች የሚውል G+3 የቢሮ  ግንባታ ሥራ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የጠቅላላ ወይም የህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ GC/BC ፈቃድ ያላቸው፡፡ የመልካም ሥራ አፈፃጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣  እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ጨረታው በሚከፍትበት ሰዓት ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  5. የጨረታ ዋጋው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የሚወዳደሩት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ፖሰታ ዉስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የግንባታ ዝርዝር መግለጫ (የግንባታውን ቴክኒካል ሰነዱን ጨምሮ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘውትር በሥራ ስዓት ከጥር 04/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታዎች በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጥር 25/05/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡በዚሁ ዕለት የጨረታ ሳጥኑ ከረፋዱ 3፡46 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ ከመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ማንኛውም ሲፒኦ የሚያቀርብ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  11. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ በለሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል፡፡ሆኖም ግን ተጫራቹ በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  12. በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚፈልጉ ከሆነ በሚወስደው የቅድመ ክፍያ የገንዘብ መጠን ተመጣጣኝ የሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ወይም አሸናፊው በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ የሚፈልግ ከሆነ ደግሞ 30 በመቶ ቅድመ ክፍያው አሰሪ መስሪያ ቤትና ተቋራጩ ጣምራ አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጎ በስራ አፈፃፀሙ መሰረት ለተቋራጩ የሚከፈል ይሆናል፡፡
  13. በጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ ማንኛውም ሲፒኦ የሚያቀርብ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  14. በተጨማሪም ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ኦርጅናል ማስረጃዎች ከውል ማስከበሪያው ጋር ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 04 34 12 63 ወይም 09 75 62 36 70 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here