የጨረታ ቁጥር፡- የጨረታ ቁጥር EPSS/10/2018
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባሕር ዳር ቅርጫፍ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ የግንባታ ሥራ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአገልግሎት መ/ቤታችን በማግኘት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በየኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቦርድ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከታህሳስ 27/2018 እስከ ጥር 18/2018 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን ጥር 19/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡10 ባሕር ዳር ከተማ ጣና ሀይቅ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮአችን ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአገልግሎታችን በአካል በመቅረብ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የግንባታ ሥራ የጠቅላላውን ዋጋ ብር 2 በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ በአገልግሎት መ/ቤታችን የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን:- 058 226 51 52
የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
ባ/ዳር ቅርንጫፍ

