ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የመርጡለማርያም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ሎት 1 የመ/ማ/ከ/አስ ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ለሚያሰራው የጌጠኛ መንገድ ኮበልስቶን ንጣፍ ሥራ ከደነቀው ተስፋው እስክ ጋሽ ፀሃው ቤት ርዝመት 255 ሜትር ስፋት 11 ሜትር እንዲሁም ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች መስፈርቱን የሚያሟሉ መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መመ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በመቅረብ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የግንባታ ሥራ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ ፊርማ ማህተም በማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥራቅ ጎጃም ዞን በመ/ማ/ከ/አስ /ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ21ኛው ቀን እስከ 4፡00 ድረስ ለጽ/ቤቱ ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመኪና መለዋወጫ ጨረታው የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን 4፡00  ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ ከላይ እንደተገለጸው ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ አንድ ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በስልክም ሆነ በአካል አቤቱታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ብር የሞሉትን ዋጋ ዜሮ ነጥብ አንድ በመቶ ሆኖ እንደ ተጫራቾች ምርጫ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ጥሬ ገንዘቡን በመሂ 1 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የተቋራጩ ደረጃ GC ወይም BC 9 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የሙያ ፈቃዱ የታደሰ መሆን አለበት፡፡
  13. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ መ/ማ/ከ/አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱ 3 ገጽ የሥራ ዝርዝር እና 1 ገጽ የዲዛይን ዝርዝር ገጽ የያዘ መሆኑን ተጫራቾች ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡

የመርጡለማርያም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here