በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር ዞን በቡሬ ከተማ የዕድገት በአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተ/ ሸራ 9× 11 በግልጽ ጨረታ ማወዳድር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ለጨረታው የቀረበውን ዝርዝር መረጃ በጨረታው ሰነድ ያገኙታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በጥሬ ገንዝብ ወይም በሚጫረቱበት ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ያለበለዚያ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ኦርጅናል ከሆነ ደግሞ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረብያ ሰነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመበት እና የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት መሆኑን በማረጋገጥ እና በፖስታ ላይ 3 ቦታ ማህተም ማድረግ በማሸግ ዩኒየኑ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ማለትም ከጥር 11/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 21/2018 ዓ.ም በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ጨረታው ሚከፈትበት ጥር 22/2018 ዓ/ም 4፡30 ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጎልም፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ጨረታው በተከፈተ አሸናፊነቱ በተገለፀበት በዕለቱ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈበት ዋጋ 10 በመቶ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዩኒየኑ ለሚከፍለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ምርቱን ዩኒየኑ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ያሉትን ለማሳያ ናሙና ከእያንዳንዱ ምርት ማሳያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ ማሟላት አለባቸው፡፡
- ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚስተናገድ ይሆናሉ፡፡
አድራሻ ቡሬ ከተማ ከዳሞት ዩኒዮን 600 ሜትር ወረድ ብሎ ወይም ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 31 74 50 /09 42 74 29 93 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
የዕድገት በአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተ

