በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ ኢ/ት/መምሪያ የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 6 ብትን ጨርቅ እንዲሁም ሎት 7 የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን መስፈርት የሚሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/መ/ገ/ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ ከጥር 11/2018 እስከ ጥር 25/2018 ዓ/ም ድረስ በመምጣት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደረበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በጠ/ወ/ገ//ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ጥር 26/2018 ዓ.ም 8:00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- በሎት 7 የተጠቀሰው የመኪና መለዋወጫ አቅርቦቱ ጋራጁ በሚገኝበት ጎንደር ከተማ መሆኑን እያሳወቅን ውሉ የአንድ አመት ኩንትራት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ድምር በመሆኑ ባዶ ቦታ ዋጋ ሳይሞሉ ማስገባት ከጨረታ ውድቅ ያደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 71 95 88 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጠገዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

