ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
29

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግንደ ወይን ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ በማክሰማ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የጽድ ዕንጨት በግልፅ  ጨረታ ለአቅራቢዎች አወዳድሮ መሽጥ  ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በ.ተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ ሂደት ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግንደ ወይን ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/ሂደት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ከጥር 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 25/2018 ዓ.ም ድረስ ማለትም እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት በግንደ ወይን ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ በ16ኛው ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው ባስመዘገበው ከፍተኛ ዋጋ ነው፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀናት የበአል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባሉት የስራ ቀናት የሚከፈት ሲሆን ሰአቱ ግን ከላይ የተጠቀሰው ይሆናል፡፡
  13. ሁሉም ተጫራቾች ከተባለው ቀን ቀድመው ካስገቡ ወይም ካመጡ የጨረታው የመጨረሻ የመክፈቻ ቀን መጠበቅ ሳያስፈልግ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  14. በማስታወቂያው ያልተጠቀሱ ነገሮች ቢኖሩ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸውን የውክልና ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  16. ዛፉ ሲቆረጥ በግቢው ውስጥ የሚገኙ በመብራት፤በቤት እና በአጥር ላይ ችግር ቢደርስ ሀላፊነቱን አሸናፊው ተጫራች ይወስዳል፡፡
  17. ማንኛውም በገቢዎችም መ/ቤቶች በኩል የሚጠየቁ ክፍያዎች ለምሳሌ እሩያሊቴና ሌሎች ክፍያዎች በተመለከተ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፡፡
  18. የእንጨቱን ብዛት እና ቦታውን በተመለከተ ከሌጁ በአካል በመጠየቅ ለማሳየት ዝግጁ ነው፡፡
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ እና ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስ.ቁ 09 22 27 78 56 ወይም 09 22 39 20 44 እና 09 48 00 54 39 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የግንደ ወይን ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here