የ2ኛ ዙር ለሶስተኛ ጊዜ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የጨረታ ቁጥር ደም/ከ/መ/ል/05/18፤ የጨረታ ዙር 2ኛ (ለሶስተኛ ጊዜ)፤ የጨረታ አይነት መደበኛ

የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ይህን አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የከተማን ቦታ ሊዝ ስለመያዝ በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል ሶስት በአንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘሩት መሠረት ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት ለሚፈልጉ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ  ከወጣበት ከጥር 13/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል በደም/ከተ/መ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ነው፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ነው፡፡
  3. ቦታውን መጐብኘት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልጽ መርሃ ግብር መሠረት የምናስጐበኝ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ በ11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተዉ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  5. በጨረታዉ የውጭ አገር ዜጎች መጫረት አይችሉም፡፡
  6. በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ አሸናፊነቱ ተገልጾ እያለ ቀርቦ ውል ያልፈጸመ በዚህ ጨረታ የማይሳተፍ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው መነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት 10 በመቶና ከዚያ በላይ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋና ሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊዉ ከተረጋገጠበት (ከተገለጸበት ) ከሚቀጥለዉ ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ወቅት ማንነታቸዉን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 44 12 29 22 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here