ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
67

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2. ህትመት፣ ሎት3. የመኪና ጎማ፣ ሎት4. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት5. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት6. የመኪና ዲኮር፣ ሎት7. የላፕቶፕ መያዣ ፖርሳ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልታችሁ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የዕቃዎችን ዓይነቶችንና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 002 ብር 100 (አንድ መቶ)  ለእያንዳንዱ የማይመለስ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የኮሚሽኑ ካርኒ  በተቆረጠበት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን የመጫረቻ ሰነዱንም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ባለሙያዎች ክፍል 007 በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ  በ4፡30  ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጐልም፣ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ  ነው፡፡ኮሚሽኑ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው ሁሉም ሎቶች በድምር ዋጋ ሲሆን ሎት 3 እና ሎት 5 በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  12. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሰለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም  በስልክ ቁጥር 058 220 03 79 መደወልና ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here