በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በደብረታቦር ከተማ የሚገኘው ጎህ ሁለገብ/የገበ/ኅ/ስራ ማህበራት ዬኒየን ኃ.የተወሰነ ከቀድሞው መገናኛ ዩኒየን ቅጥር ግቢ ውስጥ ወይም ዞን ንግድ መምሪያ አጠገብ በቁም የሚገኘውን ሁሉንም የጽድና ሌሎች የዛፍ ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ቆርጦ ለሚያነሳ ድርጅት ወይም ግለሰብ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2 በመቶ በባንክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋሰትና ከሆነ በጎህ ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከዬኒየኑ ቀርቦ የገቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ማስያዝ አለበት፡፡ ያስያዙትን የጨረታ ማስከሪያ መረጃ በሲፒኦ ከሆነ ዋናውን ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ ያስያዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ጨረታ ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ ከተሰጣቸው አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና ሲፒኦ ሲያሲዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከዬኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ስማቸውን፣ የሚወዳደሩበትን ዋጋ፣ ሙሉ አድራሻና ፊርማቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ ማህተማቸውን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥ ሲሆን በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከላይ በተገለጸው ተማሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ሆኖ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዩኒየኑ ጽ/ቤት ቀርቦ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ አስይዞ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ዛፉን በራሱ ወጭ አስቆርጦና አጓጉዞ እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ድረስ አጠቃሎ ማንሳት አለበት፡፡
- አሸናፊው ዛፉን (እንጨቱን) በሚቆርጥበትና በሚያነሳበት ጊዜ በአካባቢው በሚገኝ የመብራት መስመር፣ የስልክና ውሃ መስመር፣ በቤትና አጥር ላይ፣ በሰውና በእንስሳት ላይ፣ በመሳሰሉት ንብረቶች በስራ ላይ ችግር ወይም አደጋ ቢያጋጥም ወይም ጉዳት ቢደርስ አሸናፊው ተወዳዳሪ ኃላፊነቱን ይወስዳል ወይም ለተከሰተው ችግር ተጠያቂ ይሆናል፡፡
- ዪኒየኑ ያወጣውን ግልጽ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ወይም ግማሽ ቀን የዩኒየኑ የሥራ ቀን ነው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የዛፉን ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ ከቀድሞው የመገናኛ ዩኒየን ጽ/ቤት ድረስ ሂዶ ማየት ይችላሉ፡፡ ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 /058 141 70 12 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አድራሻ ፡- ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ዋናው ባንክ አንደኛ ፎቅ ነው፡፡
ጎሕ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

