ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ

0
31

ብሔራዊ ፓርኩ  በጋምቤላ ክልል ነው የሚገኘው:: በቀጣናው የሚገኙ የዱር እንስሳት እና መኖሪያቸውን ለመጠበቅ ነው በ1973 ዓ.ም የተመሰረተው:: አጠቃላይ ስፋቱ 4575 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል::

የባሮ ወንዝ ተፋሰስ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅ የተከለለ በመሆኑ ለዱር እንስሳቱ የተመቸ መጠለያ ሆኗል::

የፓርኩ ቀጣና በስተምሥራቅ ኮረብታ ቢኖረውም አብዛኛው ሣር እና ቁጥቋጦለበስ ሜዳ የተንጣለለበት ነው:: በመልካምድራዊ አቀማመጡ ዝቅተኛው 400 ከፍተኛው 768 ሜትር ከባህር ወለል በላይ ተለክቷል፤  የቀጣናው ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን 1,400 ሚሊ ሜትር የተለካ ሲሆን፣ ዝናብ የሚበዛበት ወቅት ከሚያዚያ እስከ ጥቅምት ያሉት ወራት ናቸው::

የዓየር ንብረቱ ሞቃታማው ከህዳር እስከ የካቲት ከ36 እስከ 400 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል:: በፓርኩ ረዣዢም ሳር ለበስ ሜዳዎች፣ በወንዞቹ ዳር ረግረጋማ ደለል የተነጠፈባቸው ዳርቻዎች እና ደንለበስ ቀጣናዎችም ተካተዋል::

የፓርኩ ቀጣና ብዛት ባላቸው የአጋዛን መንጋዎቹ ይታወቃል:: የአጋዘን መንጋዎቹ ወደ አጐራባች ሀገራት እንደሚፈልሱም ተረጋግጧል:: በድረ ገፆች::  በቀጣናው ከሚኙ ወንዞች እና ረግረጋማ ስፍራዎች 110 የዓሣ ዝርያዎች መገኘታቸው  በባለሙያዎች ተረጋግጧል::

በዓዕዋፍ በኩልም 230 ዝርያዎ ተመዝግበዋል::  የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው“ ኑቢያንጂራፍ” /ቀጭኔ/፣ ጐሽ፣ ዝሆን በወንዞች ዳርቻ መገኘታቸውም ተረጋግጧል:: ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት አፍሪካን ፓርክስ እና ናሽናል ፓርክስ አሶሴሽን ዶት ኦረግ ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 11  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here