የሂሳብ ምርመራ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
35

ንቦች ለልማት በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከጥር 1 ቀን 2025  እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2025ዓ.ም ያለውን የአንድ ዓመት በጀት ሂሳብ ህጋዊ ፈቃድ ባለው የውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ ህጋዊ ሂሳብ ምርመራ የስራ ፈቃድ ያላቸውና  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ መመሪያ መሰረት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርትፍኬት ያላቸው ኦዲተር የሆኑ፣ የሙያ ማረጋገጫ ያላቸው፣ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈለበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ አካውንቲንግና ኦዲት ቦርድ ወይም ክልል ኦዲተር መ/ቤት የ2018 ዓ.ም የታደሰ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  2. የሂሳብ ምርመራ ህጋዊ የስራ ፈቃድና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት በሚመለከተው አካል የተሰጣቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ የታደሰ የስራ ፈቃድ የሚያቀርቡ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የጊዜ ገደብ ከማለቁ በፊት በማናቸውም ጊዜ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በተመለከተ ማስተካከያ ካለው ማስተካከል ይችላል፤ ሆኖም ማስተካከያውን ጨረታው በወጣበት አግባብ ለተጫራቾች በጽሑፍ ይገልፃል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ ስምና አድራሻቸውን በኢንቨሎፕ ላይ በትክክል በመፃፍና በማሸግ ለድርጅቱ ዋና መ/ቤት ባህር ዳር ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የቴክኒክና የዋጋ መወዳደሪያውን ሰነድ ለየብቻ በተናጠል ኢንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም ተጫራቹ በራሱ ፈርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅድመ ሁኔታውን አሟልቶ በመቅረብ ውል ካልያዘ ጨረታውን በራሱ ፈቃድ እንደተሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
  12. የሂሳብ ምርመራው የሚከናወነው በመ/ቤቱ ዋና መ/ቤት ባህር ዳር ነው፡፡
  13. በስራው የሚታዩ መረጃዎች አይነት መጠን እና ከስራው የሚገኘው ውጤት ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ሥራውን ሲያጠናቅቅ በሃርድ ኮፒና በሶፍት ኮፒ ሪፖርት ለማቅረብ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈርማል፡፡
  15. ተወዳዳሪዎች ሙሉ ወጫቸውን የትራንስፖርት፣ የአበል ወጭ እና የመሳሰሉትን በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
  • የመረጃዎች ዝርዝር
ተ.ቁ የመረጃ አይነት ብዛት በኬንት ምርመራ
1 የባንክ ክፍያ ማዘዣ ሰነድ (BPV)    
2 ጆርናል ቫውቸር (JV)  
3 የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ( Receipt Voucher)  
  ጠቅላላ የቦክስ ፋይል ብዛት  

 

ከላይ የተመለከቱትን መረጃዎች ለማጠናከርና ለማረጋገጥ ሌሎች ፋይሎች፣ መመሪያዎችና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማየትና መመርመር የስራው አካል ነው፡፡

  • ተጫራቹ በጨረታው ሰነድ ላይ የተቀመጡትን መመሪያዎችና ዝርዝር መግለጫዎች በሚገባ መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  • የጨረታው ማስከበሪያ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ አይቻልም፡፡
  • የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት የጨረታው ውድድር በሁለት ደረጃ ይገመግማል፡፡
  1. የቴክኒካል ግምገማ
  • ድርጅቱ የሚያሳትፋቸው ባለሙያዎች ልምድ፣ ሙያና የት/ደረጃ 45በመቶ፡፡
  • ድርጅቱ ባለፉት ቅርብ ዓመታት የመረመሯቸው 5 ተቋማት የመልከም ስራ አፈፃፀም25 በመቶ፡፡
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ወይም ታክስ፣ የውሎ አበልና ትራንስፖርትን ጨምሮ 30 በመቶ፡፡
  • ለቴክኒክ ግምገማ ከ70 በመቶ እና ለዋጋ ከ30በመቶ የተገኘው ውጤት ተደምሮ 1ኛ የሚሆነው አሸናፊ  ይሆናል፡፡
  • ውድድሩ በቴክኒክና በዋጋ የነጥብ ድምር ውጤት መሠረት ሆኖ ለዋጋ የሚሰጠው ውጤት የሚሰላው በሚከተለው ቀመር መሠረት ነው፡፡

ዉጤትን በተመለከተ ከቴክኒካል ዉጤት ዉስጥ 50በመቶ እና ከዚያ በላይ ዉጤት ያመጡ ተወዳዳሪዎችን በመለየት ዝቅተኛ ነጥብ ያመጣ የዉድድሩ አሸናፊ ይሆናል፡፡ የሰው ሀይል ስምሪት በሂሳብ ምርመራ ስራ ላይ የሚያሳትፉቸውን ባለሙያዎች ብዛት የት/ደረጃ የሙያ አይነትና በሙያቸው ያላቸውን ልምድ ከዚህ ጋር በተያያዘው ቅጽ ላይ በማያሻማ ሁኔታ መሞላት ይኖርበታል፡፡

  • በኦዲት ስራው ከሚሰማሩት ባለሙያዎች የቡድን መሪ በአካውንቲንግ ቢ.ኤ ያለውና ACCA (Association of Chartered Certified Accountants) CIA (Certified Internal Auditor) CPA Certified Public Auditor ቢያንስ 6 ዓመት በኦዲት ስራ የሠራ ሊሆን ይገባል፡፡
  • ሌሎች ረዳቶቹ ቢያንስ በአካውንቲንግ ዲኘሎማና ከ6 ዓመት በላይ በኦዲት ስራ ያገለገሉ መሆን አለባቸው፡፡
  • የቡድኑ አባላት ቡድን መሪውን ጨምሮ ከ3 ማነስ የለባቸውም፡፡
  1. የስራ ኘሮግራምና የአከፋፈል ሁኔታ፡፡
  • የበጀት ዓመቱን ሂሳብ መርምሮ ለማጠናቀቅና ሪፖርት ለማቅረብ የሚፈጅበት ጊዜ ከሚያሰማራው የስው ሀይል ጋር ተገናዝቦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ቢሆኑ ስራውን የሚጀምሩበትና የሚያጠናቅቁበትን ቀናት በግልጽ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. በፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ወይም በክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ወይም በሚመለከተው አካል የተሰጠው የደረጃ ምደባ የሚያሳይ መረጃ ፎቶ ኮፒ ከኦርጅናሉ ጋር ተገናዝቦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. የመወዳደሪያ ዋናውን ለይቶ የአገልግሎት፣ የታክስ፣የውሎ አበልና ትራንስፖርቴሽን ወጪ በማጠቃለል ከዚህ ጋር አባሪ በተደርገው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ማንኛውም ወጪ በኦዲት አገልግሎት ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡ በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ላይ የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው ስም፣ ፊርማና ማህተም መኖር አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ እና በግልጽ ሁኔታ በተሰየመ ሽፋን ውስጥ፣ ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሠረት መረጃዎቹን በትክክል አሟልተዉ እንዲያቀርቡ።የጨረታ ሰነዶቹ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን፣ በባህር ዳር ሙሉ በለው ህንፃ፣ ሁለተኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ፣ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ለበለጠ መረጃ 0583205204 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፤

 

ንቦች ለልማት በኢትዮጵያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here