ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

በምዕ/ጐጃም/ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የተለያዩ ጨረታዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ሎት1. ሶፍትዌሮችን ጂፒኤስ ግዥ ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣ ሎት3. የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ፣ ሎት4. የተለያዩ የአለባሳት ግዥ፣ ሎት5. ህትመት ግዥ፣ ሎት6. የአትክልት ዘር ቀይ ስርና ካሮት ሽያጭ ፣ ሎት7. የፋብሪካ መለዋወጫ እቃዎች ግዥ፣ ሎት8. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ፣ ሎት9. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ግዥ፣ ሎት10. የሰብል መደርደሪያ ፓሌት ግዥ ብዛት 100፣  ሎት11. መጋረጃ ቁሳቁስ ከነእጁ እና ምንጣፍ ግዥ ለአራተኛ ጊዜ የወጣ ሎት12.የዱቄት ፋብሪካ ሙሉ ሰርቢስ ማሰራትና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ማነኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  3. የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ወይም ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ሁለት በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ወይም በጥሬ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታው ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በፓስታው ውስጥ ማስገባት እና ፓስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ በተገለፀው መሰረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በማዘጋጀት ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን  እስከ 8ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እና  በ8ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ  የመክፈቻ ቀን በእለቱ  በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  10. የንግድ ፍቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  11. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ድምር 10በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  1. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 640/1032 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  5. ማሳሰቢያ፡- የጨረታው የመክፈቻ ቀን በአል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

 

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here