የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፈርኒቸር እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች እና የጽዳት እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ቲን ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ 200 ብር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 102 ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከጥር 11/2018 ዓ.ም ወጥቶ የሰነድ ሽያጭ ከጥር 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት ጥር 23/2018 ዓ.ም 6፡30 ያታሸገል ፡፡ ጥር 25/2018 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 0582181424 /0582180644 /0582180075 መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

