ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በeTAS በጀት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ እና በመደበኛ በጀት የህንፃ ጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ነጥቦች እንደሚከተለው ተገልፀዋል፡፡ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ብር 450,000 (አራት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና የቢሮ ህንፃ ጽዳት ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር )ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አብክመ ገቢዎች ቢሮ ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር 313 ኤሌክትሮኒክስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የህንፃ ጽዳት አገልግሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  7. አስራ ስድስተኛው (16ኛዉ) ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰአት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
  9. ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

አድራሻችን፡- ባሕር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ጀርባ እና የድሮው ዶ/ር ፍሬው የነበረው የአሁኑ ዶ/ር አዲሱ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 መጠቀም ይችላሉ፡፡

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here