ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
38

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አርማጭሆ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የገዥና ንብረት አስተዳደር በመንግስት ግምጃ ቤት ለዉሃ ግንባታ አገልግሎት የሚዉሉ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  4. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16 ተኛው ቀን 3፡29 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት ክፍል በቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 3፡45 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በራሳቸው ምክንያት በጨረታ ከፈታ ባይገኙም የጨረታ ፖስታ በመክፈት ውድድሩ የሚካሄድ ሲሆን እነሱም በወቅቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በአል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እና በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 65 33 96 /09 18 15 46 34 መደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ አርማጭሆ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here