ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በኮዋሽ ፕሮጀክት ከተያዘ በጀት ለዉሃ ግንባታ አገልግሎት የሚዉሉ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈልከ ገንዘብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16 ኛው ቀን 3፡29 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት ክፍል በቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 3፡45 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በራሳቸው ምክንያት በጨረታ ከፈታ ባይገኙም የጨረታ ፖስታ በመክፈት ውድድሩ የሚካሄድ ሲሆን እነሱም በወቅቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በአል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እና በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 16 65 33 96 /09 13 15 46 34 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here